Subscribe : ኑሮን በዘዴ / @ኑሮንበዘዴ ደንበኛችን ይሁኑ ፡፡
ፎሮፎር በሁሉም የእድሜ ክልል ላይ የሚከሠት ችግር ቢሆንም በበለጠ መልኩ ግን ወጣቶችና ጐልማሶች ለችግሩ ተጋላጮች ናቸው፡፡ የተለያዩ ጥናቶች ወንዶች ከሴቶች በበለጠ በፎሮፎር እንደሚጠቁ አሣይተዋል፡፡በተለያዩ የፀጉር መንከባከብያ ምርቶች ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ ኬሚካሎች በተለይም በጄሎች፣ እስኘሬዎች፣ ሻምፖዎችና ቅባቶች ውስጥ የሚገኙ ኬሚካሎች ከቆዳችን አይነት ጋር ላይስማሙ ስለሚችሉ አለርጂኮችን ይፈጥራሉ በዚህም ምክንያት የጭንቅላት ቆዳ ላይ መቅላት፣ መቁሠልና ማሣከክ የመሣሠሉት ሁኔታዎች ይኖራሉ፡፡ ይህም ፎሮፎርን ለማባባስ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ይታወቃል፡፡ በመሆኑም እነዚህን ምርቶች ስንጠቀም እንደቆዳችን አይነት የሚስማማንን በአግባቡ መርጠን መሆን ይኖርበታል፡፡
コメント