Loading...
「ツール」は右上に移動しました。
利用したサーバー: balsam-secret-fine
70いいね 624回再生

#Live#ቀጥታሥርጭት 🔴 ሚያዝያ 2‼️ኪዳን እናድርስ♦️ ልደታ ማርያም ወሩን ትባርክልን#ከጎፋ_ቅዱስመርቆሬዎስ

ይህንን ያውቃሉ ?
👇 👇 👇
አቡነ_ሕርያቆስ_ዘብሕንሳ

በግንቦት 1 ቀን የከበረ አቡነ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ የእመቤታችንን ቅዳሴ የደረሰበት ነው፡፡ ሕርያቆስ ማለት ‹‹ኅሩይ-የተመረጠ›› ማለት ነው፡፡ እንዲሁም ደግሞ ምሥጢረ ሥላሴን ከሁሉ ይልቅ አራቆ ይናገራልና አባቶቻን ሕርያቆስ ማለት ‹‹ረቂቅ›› ማለት ነው ይሉታል፡፡ ‹‹አብ ፀሐይ ወልድ ፀሐይ መንፈስ ቅዱስ ፀሐይ›› ብሎ አመስግኗልና አሁንም ሕርያቆስ ማለት ‹‹ፀሐይ›› ማለት ነው ይሉታል፡፡ ደግሞም የምእመናንን ልቡና በትምህርቱ ብሩህ አድርጓልና ሕርያቆስ ማለት ‹‹ብርሃን›› ማለት ነው፡፡ አንድም ደግሞ ሕርያቆስ ማለት ‹ንብ› ማለት ነው፡፡ ንብ የማትቀምሰው አበባ እንደሌለ ሁሉ ሕርያቆስም ያልቀሰመው ሰማያዊ ዕውቀት የለምና እርሱን የማይጠቅሰው ሊቅ የለም፡፡

አባ ሕርያቆስ ስለ ምሥጢረ ሥላሴ እና ስለ ምሥጢረ ሥጋዌ የሚያመሰጥረውን እመቤታችንን በተለያዩ ምሳሌያት እየመሰለ የሚያመሰግንበትን ድንቅ የሆነውን ድርሰቱን ‹‹ቅዳሴ ማርያምን›› ሰማያዊ ምሥጢር ወለል ብሎ ተከፍቶለት ደርሶታል፡፡ የብሕንሳው ኤዺስቆዾስ ስላረፉ በእሳቸው ምትክ የሚሾሙትን ሲያፈላልጉ መንፈስ ቅዱስ አባ ሕርያቆስን መረጣቸው፡፡ የከበሩ ሐዋርያት ‹‹የተማረና ግብረ ገብ የሆነ ይሾም›› ብለው ሥርዓት ሠርተዋል፡፡ ደግሞም ‹‹ሁለቱን አስተባብሮ የያዘ ባይገኝ የተማረ ከሆነ ይሾም›› ብለዋል፡፡ ምክንያቱም በትምህርቱ መናፍቃንን ተከራክሮ ይመልሳልና ነው፡፡ ደግሞም ‹‹ግብረ ገብም ከሆነ ይሾም›› ብለዋል፡፡ ምክንያቱም በጸሎቱ ይጠብቃል በትሩፋቱ ያጸድቃልና ነው፡፡ በዚህም መሠረት አባ ሕርያቆስ ያልተማረ ነገር ግን ግብረ ገብ ነውና ‹‹ትምህርቱን ውሎ አድሮ ያደርገዋል›› ብለው ሾሙት፡፡ አባ ሕርያቆስም የተማረው ለጸሎት ለቅዳሴ ያህል ትንሽ ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ ይህ ቅዱስ አባት በብሕንሳ ገዳም በ10000 መነኮሳት እና በ10000 መነኮሳይያት ላይ ተሹሞ የገዳሙ አስተዳዳሪ ሆነ፡፡

አባ ሕርያቆስ እመቤታችንን እጅግ ከመውደዱ የተነሣ ስሟን እንኳን ሲጠራ በመስጦ ልቡናው ይሰወርበት ነበር፡፡ ዘወትር ፍቅሯ ከማሰብ በቀር ሌላም አያስብም ነበር፡፡ እርሱ የነበረበት ዘመን የሊቃውንት ዘመን ስለነበር ሁሉም ለትምህርት ሲተጉ አባ ሕርያቆስ ግን ለጸሎትና ለደግነት ብቻ ይተጋ ነበር፡፡ የአባ ሕርያቆስ የሌት ተቀን ሞኞቱ ‹‹እንደ ቅዱስ ኤፍሬም የእመቤታችን ምስጋና እንደ ባሕር አሸዋ እንደ ሰማይ ኮከብ በዝቶልኝ እንደልብስ ለብሼም እንደ ምግብ ተመግቤው›› የሚል ነበር፡፡ ከልጅነቱ ጀምሮም እጅግ ስለሚወዳት እመቤታችንም ትጠብቀው ነበር፡፡ ከዕለታት በአንደኛው ቀን አባ ሕርያቆስ በበረኃ ብቻውን እየተጓዘ ሳለ የእመቤታችንን ፍቅር በልቡ ሲያመላልስ ስሟን እያነሣ ሲዘምር በተመሥጦ ውስጥ ሆኖ መንገድ ሳተና ከታላቅ ገደል ጫፍ ደርሶ ሳያስበው ወደቀ፡፡ ከገደሉም ጫፍ ደርሶ ከወደቀ በኋላ እጅግ ደንግጦ ራሱን ቢመለከት አካሉ ሳይጎድል ልብሱ ሳይቆሽሽ አገኘው፡፡ በዚህም ተገርሞ ያለበትን አካባቢውን ቢያማትር ራሱን ብርሃንን በተሞላ የልብስ ዘርፍ ላይ አገኘው፡፡ ያም ብርሃንን የተሞላ የልብስ ዘርፍ የእመቤታችን የቀሚሷ ዘርፍ ነው፡፡ በዚህም እጅግ ደንግጦ ‹‹እመ ብርሃን›› ብሎ ጮኸ፡፡ እመቤታችንም ከፊቱ ቁማ ተገለጠችለት፡፡ እርሱም የብርሃን እናቱ ድንግል ወላዲተ አምላክን በገሃድ በዐይኑ አጠገቡ ቆማ ቢያያት በደስታ ዘለለ፡፡ እመቤታችንም በቃሏ አነጋግራው ባርካው ተሰወረችው፡፡ እርሱም ፍቅሯ ጣዕሟ ቢመስጠው ከሰው ሳይገናኝ ምግብም ሳይበላ እዚያው እገደሉ ውስጥ አንድ ዓመት በምስጋና ብቻ በተመስጦ ኖሯል፡፡ በኋላም እመቤታችን ድጋሚ ተገልጣለት ከገደሉ አውጥታ ወደ ሀገሩ አድርሳዋለች፡፡

ከዚህም በኋላ አባ ሕርያቆስ እርሱ በተሾመባ በብሕንሳ ገዳም ሴትና ወንድ ያልተለየባት ገዳም ነበረችና በዚህች ገዳም የተሾመው አባ ሕርያቆስ ብዙም ትምህርት ስላልነበረው ይንቁት ነበር፡፡ ‹‹ከመጠምጠም መማር ይቅደም›› እንዲሉ ‹‹ከመሾም በፊት መማር አይቀድምም›› እያሉም ይዘብቱበት ነበር፡፡ እርሱ ግን እንደጠሉኝ ልጥላቸው ሳይል በፍቅር በትሕትና ይመክራቸው ነበር፡፡ እነርሱ ግን ‹‹በምን ምክንያት እንሻረው›› እያሉ ይመክሩ ነበር፡፡ ከዕለታት በአንድ ቀን ‹‹ቀድሰህ አቁርበን እንበለውና አይሆንም ካለን በዚህ ምክንያት እንሻረው?›› ብለው መከሩ፡፡ እርሱም ሥርዓተ ቅዳሴውን ፈጽሞ ወደፍሬ ቅዳሴው ሲደርስ የትኛውን ከባድ ቅዳሴ ቀድስ እንበለው?›› እያሉ ይመካከሩ ጀመር፡፡ እርሱ ግን ከቅዳሴ ሐዋርያት በቀር የሚያውቀው አልነበረም፡፡ አባ ሕርያቆስ እያዘነ ወደ መንበሩ ዞሮ ‹‹እመቤቴ ሆይ! መናቄን መገፋቴን ተመልከች›› ሲል ወዲያው እመቤታችን ወርዳ ጠራችውና በዘርፋፋው ቀሚሷ ላይ ረቂቅ የሆነ ቅዳሴን አሳየችው፡፡ የለመኗትን የማትነሣ፣ የነገሯትን የማትረሣ የብርሃን እናቱ እመቤታችንም የልቡን መሻት ተመልክታ ‹‹ጎስዐ ልብየ ቃለ ሠናየ ልቡናዬ በጎ ነገርን አወጣ›› በማለት ጀምሮ ‹‹ዛሬም አብን ወልድንና መንፈስ ቅዱስን እናመስግን›› እስከሚለው ድረስ ሰተት አድርጋ አስደርሳዋለች፡፡ እነርሱም ይህንን ግሩም የሆነውን ቅዳሴውን አደነቁ፡፡

የሚንቁትና የሚጠሉት ‹‹ይህ የነገሩትን ቀለም እንኳን አከናውኖ መናገር የማይችል ዛሬስ እንግዳ ድርሰት እደርሳለው ብሎ አገኝ አጣውን የቆጥ የባጡን ይቀባጥራል›› ብለው ተደነቁበት፡፡ የሚወዱትና የሚያከብሩት ግን ‹‹ከመንፈስ ቅዱስ ነው እንጂ እንዲህ ያለ ምሥጢር ከእሩቅ ብዕሲ ይገኛልን!›› ብለው አደነቁለት፡፡ ወዲያው የሚወዱት የሚያከብሩት ‹‹ጽፈን ደጉሰን አንይዘውምን!?›› አሉ፡፡ የሚንቁት የሚጠሉት ደግሞ ‹‹ማን ተናገረው ብለን እንይዘዋለን?›› አሉ፡፡ እንደ ልማዱ አድርገን አንይዘውም አሉ፡፡ ለሃገራቸው እንግዳ ድርሰት የተደረሰ እንደሆነ ጽፈው ደጉሰው ከእሳት ይጥሉታል፡፡ ከእሳት ደህና ሆኖ የወጣ እንደሆነ ከውሃ ይጥሉታል፡፡ ከውኃም ደህና ሆኖ የወጣ እንደሆነ ከድውይ ሰው ላይ ይጥሉታል፡፡ ከእሳት ገብቶ ባይቃጠል፣ ከውኃ ገብቶ ባይርስ በመጨረሻም ድውይ የፈወሰ እንደሆነ ‹‹ደገኛ ድርሰት ነው›› ብለው ይይዙታል፡፡ ይህንንም ቅዳሴ ማርያምን ጽፈው ደጉሰው ከእሳት ላይ ጣሉት፣ ከእሳት ደህና ወጣ፡፡ ከውኃ ላይ ጣሉት-ከውኃ ደህና ሆኖ ወጣ፡፡ ከደውያን ላይ ጣሉት-ድውይ ፈወሰ፡፡ ይልቁንም ሙት አስነሣ፡፡ ከዚህም በኋላ ‹‹ደገኛ ድርሰት ነው›› ብለው ጽፈው ደጉሰው ይዘውታል፡፡ በጥራዝም 14ኛ አድርገው ጠርዘውታል፡፡ ቅዳሴ ከዚያ በፊት 13 ነበርና አሁን ግን 14ኛ አድርገው ጽፈውታል፡፡ በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ከ14ቱም ቅዳሴ ተአምራት ያልተደረገበት የለ

コメント