Subscribe:ኑሮን በዘዴ / @ኑሮንበዘዴ ደንበኛችን ይሁኑ ፡፡
ካፌይን አዕምሮን ለማነቃቃት የሚረዳና በተለይ በቡና፣በሻይ እና በተለያዩ የለስላሳ መጠጦች ውስጥ በስፋት የሚገኝ ኬሚካል ነው፡፡ካፌይን ከእነዚህ መጠጦች በተጨማሪ በቸኮሌቶች ፣በብስኩቶች እና በተለያዩ የህመም ማስታገሻና የራስ ምታት መድሀኒቶች ውስጥ ይገኛል፡፡ይህ ኬሚካል ሱስ የማስያዝ ባህሪው ከፍተኛ ነው፡፡ እነዚህ መጠጦችና ምግቦች እንዲሁም መድሀኒቶች ካፌይን የመያዝ አቅማቸው እንደየሁኔታው የተለያየ ሲሆን በቡና ውስጥ የሚገኘው የካፌይን መጠን ግን ከፍ ያለ ነው፡፡ይህም አንድ ሲኒ ቡና ከ100-150 ሚ.ግ ካፌይን በውስጡ ይይዛል ፡፡ልላው አንድ ሰው በቀን በአማካይ 80 ሚ.ግ ካፌይን እንደሚወስድ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ታዲያ ከመጠን ያለፈ ካፌይንን መጠቀም ለከፋ የጤና ችግር ያዳርጋል፡፡በካፌይን ሳቢያ ከሚከሰቱ የጤና ችግሮች መካከል የሚከተሉት ተጠቃሽ ናቸው፡፡
፦የእንቅልፍ ማጣት
፦ጭንቀት
፦ራስ ምታት
፦ድብርት
コメント