💠ደብደረ ዘይት💠
ደብረ ዘይት የዓቢይ ጾም አምሥተኛ ሳምንት ነው ።
ደብረ ዘይት ከኢየሩሳሌም ከተማ በስተምሥራቅ በኩል የሚገኝ ኮረብታማ ቦታ ነው።
ቦታው የወይራ ዛፍ የሞላበት ተራራማ ሥፍራ ነው።
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጸለየበትና እመቤታችን ድንግል ማርያም የተቀበረችበት ጌቴሴማኒ የተባለውም የአትክልት ሥፍራ በዚያ ይገኛል
በዚህ ዕለት ነገረ ምጽዓቱ ይታሰባል
ጌታ በደብረ ዘይት ተራራ ተቀምጦ ሳለ ደቀመዛሙርቱ ወደእርሱ ቀርበው የመምጣትህና የዓለም መጨረሻ ምልክቱ ምንድነው ንገረን ብለው ጠየቁት
እርሱም እንዲህ አላቸው ብዙዎች እኔ ክርስቶስነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉ
ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ።
ጦርንም የጦርነትንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ አትደንግጡ
ዳሩ ግን መጨረሻው ገና ነው
ሕዝብ ሕዝብላይ መንግሥት በመንግሥት ላይ ይነሳሉ
ረሀብ፣ቸነፈር፣የምድር መነዋወጥ በልዩ ልዩ ሥፍራይሆናል እነዚህ ሁሉ የምጥ መጀመሪያ ናቸው አላቸው።
በዚህ ዕለት በመዝ 49፦ቁ 2 ላይ የሚገኘውን የዳዊት መዝሙር ዲያቆኑ እንዲህ በማለት ይሰብካል
➡️ እግዚአብሔርሰ ገሀደ ይመጽእ
ወአምላክነሂ ኢያረምም
እሳት ይነድድ ቅድሜሁ።⬅️
➡️ እግዚአብሔር ግልጥ ሆኖ ይመጣል
አምላካችን ይመጣል
ዝምም አይልም
እሳት በፊቱ ይነዳል፤⬅️
የቅዱስ ማቴዎስ ወንጌል ም/24፣ቁ44 በዕለቱ የሚነበበው የወንጌል ክፍል ነው
ጌታችሁ በየትኛው ሰዓትበየትኛው ቀን እንደሚመጣ አታውቁምና ተዘጋጅታችሁ ኑሩ ይላል።
እኛም የወንጌሉን ቃል በማስታወስ ንስሐ ገብተን ተዘጋጅተን እንድንኖር
የእግዚአብሔር ቸርነት ፣
የድንግል ማርያምአማላጅነት፣
የቅዱሳን መላእት ጥበቃ፣
የጻድቃን የሰማዕታት ምልጃና ጸሎት፣
አይለየን
✝ አሜ
コメント